Food Items and Drinks
የሰበታ መርሐ ዕዉራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች በ2019 ዓ.ም መደበኛ በጀት የተለያዩ የምግብ አይነቶችን፣ እስቴሽነሪ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ማገዶ (ግንዲላ)፣ እና የደንብ ልብስ ስፌት ለማቅረብ ፍቃድ ያላቸው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰበታ መርሐ ዕዉራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች በ2019 ዓ.ም መደበኛ በጀት የተለያዩ የምግብ አይነቶችን፤ እስቴሽነሪ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፤ ማገዶ (ግንዲላ)፤ እና የደንብ ልብስ ስፌት ለማቅረብ ፍቃድ ያላቸው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. የተዘጋጀውን የምግብ እና ከላይ ዝርዝር የያዘ የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 150.00 በመክፈል ከት/ቤቱ ሂሣብና በጀት የቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በተጠቀሱት የዕቃ አይነቶች የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በ2018 ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የገበሩ፣ የቫት ተመዝጋቢና ከላይ የተጠቀሱትን የዕቃ ዝርዝር ዓይነቶች አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።
3. . ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመክፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ አቅርቦት ለሚከፍሉበት ንግድ ዘርፍ በጥሬ ብር ወይም በቼክ 150,000.00 (መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በት/ቤቱ የባንክ ሂሣብ ቁጥር፤ 1000016086006 ገቢ በማረግ በካሽ ወይም በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን የተጠቀሱትን የዕቃ ዝርዝር በገዙት የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ የሚያቀርቡበትን ዋጋ ግልጽ በሆነ የእጅ ጽሑፍ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተጫራቹ ድርጅት ማህተምና የድርጅቱ ሀላፊ/ተጫራቹ ፊርማ /ተረጋግጦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 2 ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
5. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 2 ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
6. በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ድርጅት የሚያስገባውን የተጠቀሱትን የዕቃ ዝርዝር ዋጋ ከመቶ አስር 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት።
7. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ማሳሰቢያ፦ሥጋ ፣ ዳቦ፤ የጤፍ ዱቄት ከሰበታ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 338 0006 ደውሎ መጠየቅ ደቻላል።
የሰበታ መርሐ ዕዉራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: የሰበታ መርሐዕውራን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: 150,000.00 (መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ለእያንዳንዱ አቅርቦት
- Bid document price: 150.00 (አንድ መቶ ሃምሣ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T11:30:30.000Z