Machinery and Equipment
ጣና ፍሎራ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በእጅ የሚገፋ ትራክተር በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
Description
ለ2ኛ ጊዜ በድጋሚ የወጣ በእጅ የሚገፋ ትራክተር ግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ በ124 ሄክታር ላይ በአበባ፣አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን ለእርሻ ልማቱ አገልግሎት የሚውል በእጅ የሚገፋ ትራክተር በጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ኩባንያው ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- Super DI power tiller hand working tractor_model DI 120, 12 hp, rpm 2000, cc 744 total weight 502kg
- full tanker capacity 10.7 L
- model DI 120 ተጨማሪ ስፔሲፊኬሽኖችን በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ያገኙታል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው::
3. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
4. የተ. እ ታ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ቅጹን) የማይመለስ ብር 300 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከኩባያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ በጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር ስም በተሰራ ሲፒኦ ለሚጫረትበት ግዥ ከተቀመጠው የመጫረቻ ዋጋ 2% ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
8. ተጫራቾች ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በመገኘት የዋጋ ማቅረቢያ ቅጹን መውሰድ ይችላሉ፡፡
9. ጨረታው ከወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/ የግ/ማህበር ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913 696 383/ 0918 481 598 ወይም 058 220 4798 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
11. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
12. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ጣና ፍሎራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ድረስ በመቅረብ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
13. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
14. ኩባንያው ውሉን እንደየአስፈላጊነቱ በየስድስት ወሩ ሊያድስ ይችላል፡፡
15. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ-የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ: ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሀይሌ ት/ቤት ጎን፣ ስልክ ቁጥር 0582204798፣
ኢሜል፡ [email protected] , ....
ጣና ፍሎራ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Tana Flora P.L.C.
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T11:47:56.000Z