Building Construction

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ//ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 01,04 እና 07 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 1/2019

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ//ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 01,04 እና 07 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ስስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

ሎት

የፕሮጀክት ስም

ወረዳ

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

አድራሻ

1

ብሩህ ተስፋ 1 ደረጃ /ቤት የመማሪያ ክፍል

01

2%

ደረጃ 6 ብቻ

90 ቀን

ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ

2

ቴራዞ ንጥፍ ስራ

07

2%

ደረጃ 7 እና 8 ብቻ

90 ቀን

3

ኮብል ጥገና

04

2%

ደረጃ 8 ብቻ

90 ቀን

1. ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የ2018 ዓ.ም የከፈሉ፤ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ፣ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ አራት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፤ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BlD BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 2 ፖስታ የፋይናንሻል እንዲሁም ቴከኒካል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፤ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል)።

3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት (work Days) ቅዳሜን ጨምሮ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረት ልማት በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን (work Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 16 ኛው የስራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

4. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጣነ (unbalanced rate) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል።

5. ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።

6. በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።

7. እጃቸው ላይ ምንም አይነት ስራ እንደሌላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ስራም ካላቸው 75% መድረሱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡ ጨረታ መሳተፍ የሚቻለው በአንድ ሎት ብቻ ነው

8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ ፡-

  • የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረተ ልማት ቡድን በጹሑፍ ጥያቄ መቅረብ ይችላሉ።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ//ፍ/ማ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን (work Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-04 10:30
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን (work Days) ጠዋት 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ//ፍ/ማ/ጽ/ቤት
  • Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T13:36:31.000Z
← Back to all tenders