House and Building Foreclosure

የቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ግርማዬ በላይ እና በፍርድ ባለእዳ እነ ወ/ሮ አስናቀች መንገሻ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ319842 በቀን 17/11/2017ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.329695 በቀን 27/06/2018ዒም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ

1ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 066 እና 068 የሆነው የውርስ ሀብት የቤት ቁጥር 066 የተመዘገበው በወ/ሮ የሺወርቅ ወ/ገብርኤል ስም የተመዘገበ ይዞታው ገና መብት ያልተፈጠረለት ቢሆንም በ1988ዓ.ም የአየር ካርታ ጂ.አይ.ኤስ/የይዞታ ስፋት 84ካ.ሜ የቤቱ ቤቱ/ቦታው/ በ4ቱም አቅጣጫ ያሉ አዋሳኞች በሰሜን የቤት ቁጥር 64 ፣በደቡብ የቤት ቁጥር 68 ፣በምስራቅ የቤት ቁጥር 62 መንገድ ፣በምእራብ የቤት ቁጥር 69 ለሶስተኛ ወገን ስም ንብረት ዝውውር ለማድረግ መብት ያልተፈጠረለት ይዞታ ነው ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,564,552 (ሶስት ሚሊየን አምስት መቶ ስልሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ የቤት ቁጥር 068 የተመዘገበው በወ/ሮ ምትኬ ሙሉጌታ ወ/አብ ስም የተመዘገበ ይዞታው ገና መብት ያልተፈጠረለት ቢሆንም በ1988ዓ.ም የአየር ካርታ /ጂ.አይ.ኤስ የይዞታ ስፋት 101ካ.ሜ የቤቱ ቤቱ/ቦታው በ4ቱም አቅጣጫ ያሉ አዋሳኞች በሰሜን የቀበሌ ቤት፣በደቡብ የቀበሌ ቤት፣በምስራቅ የቀበሌ ቤት መንገድ ፣በምእራብ ስዩም ማሞ ለሶስተኛ ወገን ስም ንብረት ዝውውር ለማድረግ መብት ያልተፈጠረለት ይዞታ ነው ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,272,378 (አራት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 15/2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል።ከ1/4ኛ ኦስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሓራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-25
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-25 11:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
  • Posted at: 2026-08-19T11:32:35.000Z
← Back to all tenders