Spare Parts and Car Decoration Materials

በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው የወረዳዉ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት አመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው የወረዳዉ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት አመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፤

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው፣

3. የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ኦሪጂናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።

6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።

7. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፣

8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይቻላል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 15% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

10. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦሪጂናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት።

11. አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስዝ ይሆናል።

12. ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ በሎት ድምር ነው።

13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

14. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል። በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።

15. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 71 69 22 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

16. በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ

አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች/ኦርጅናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው እንዲሁም በየፑሉ በሚገኘው ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።

በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-09 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 15%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
  • Posted at: 2026-08-19T13:12:42.000Z
← Back to all tenders