House and Building Sale
የመኖሪያ ቤቶች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ሞገስ ገብሬ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ኢብሳ ድዶ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 158884 በ13/06/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 173767 በ24/04/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት 1ኛ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ስሙ 72 አካባቢ ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር ቦሌ 15-1/92/4/14/86470/00 የሴሪያል 07125820 የቦታ ስፋት 500ካ/ሜ በወ/ሮ ቤቲ ድርቤ ረጋሳ ስም የተመዘገበ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 11,002,500 ( አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
2ኛ በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ስሙ 72 አካባቢ ውስጥ የሚገኝ የካርታ ቁጥር ቦሌ 15-1/92/4/14/86175/00 የሴሪያል 07125825 የቦታ ስፋት 500ካ/ሜ በኢብሳ ድዶ ዳሮ ስም የተመዘገበ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 11,007,500 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሰባት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ቤቶቹ በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስም 72 አካባቢ አዋሳኞቹም በሰሜን መንገድ በምስራቅ የአቶ ገብሬ እና በምዕራብ መንገድ የሆነ የቦታቸው ስፋት 1000ካ/ሜ ይዞታ ላይ ያረፉ ሁለት ቤቶች ናቸው ይዞታው ደራርቱ አደባባይ ሰሚት አካባቢ ቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ ቦሌ ቪ አያፒተርሚናል የኮሪደር ክልል ውስጥ የገባ መንገድ የማይነካው ቢሆንም ነገር ግን በሰሜን 60ካ/ሜ መንገድ የሚያዋስነው ሆኖ በግንባታ ጊዜ ወይም በኮሪደር በሚተገበርበት ወቅት 10 ሜትር ሴትባክ ለመጠበቅ 10 ሜትር ወደ ይዞታው የሚገባ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት CPO አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሽጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-28 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T14:17:21.000Z