Vehicle

የባህር ዳር ከተማ የመ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት አንድ ተሽከርካሪ መኪና ሾፌር ነዳጅ እና የጥገና አገልግሎት አከራይ ሸፍኖ የሚወዳደር ድርጅቶችን (ግለሰቦችን) በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለ1 አመት ለዋናው መስሪያ ቤት እና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ሰርቪስ መኪና መከራየት ይፈልጋል

Description

ለሠራተኞች ሰርቪስ መኪና ኪራይ ማስታወቂያ

የባህር ዳር ከተማ የመ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት አንድ ተሽከርካሪ መኪና ሾፌር ነዳጅ እና የጥገና አገልግሎት አከራይ ሸፍኖ የሚወዳደር ድርጅቶችን (ግለሰቦችን) በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለ1 አመት ለዋናው መስሪያ ቤት እና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚሰጥ ሰርቪስ መኪና መከራየት ይፈልጋል።

ስለዚህ መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት ተሽከርካሪውን ማከራየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)  ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ለኪራይ የቀረበውን ተሽከርካሪ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. በየወሩ የአገልግሎት ክፍያው ሲፈፀም ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6. የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ)100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር)  ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7. የሚንቀሳቀሱበት ፌርማታ(ቦታዎች) መ/ቤቱ (ድርጅቱ) በሚያቀርበው ፌርማታ ዝርዝር መሰረት ይሆናል፡፡

8. ሞዴላቸው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2011 እና በላይ ያለና፤ የወንበር ልብሱ የተሻለ መኪና ለድርጅታችን ለማከራየት የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 207 ገዝቶ በመውሰድ መጫረት ይቻላል፡፡

9. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን(ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የዋጋ ማወዳደሪያ ፖስታዎች በማሸግ በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 202 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያላቀረበ ተወዳዳሪ ወይም  ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል::

10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው 
የስራ ቀን በ8፡30  ይከፈታል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 70 59 በመጠቀም መደወል ይቻላል፡፡

የባህር ዳር ከተማ የመ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት

ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Bid opening: 2026-08-31 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bahir Dar City Water and Sewerage Service
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T06:55:38.000Z
← Back to all tenders