Insurance Service

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አመታዊ የተሽከርካሪ እና የሶስተኛ ወገን ሙሉ ሽፋን የመድን ዋስትና (ኢንሹራንስ) አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አመታዊ የተሽከርካሪ እና የሶስተኛ ወገን ሙሉ ሽፋን የመድን ዋስትና (ኢንሹራንስ) አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1. በዘርፉ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤

4. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የአገልግሎቱ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የስራውን(የአገልግሎቱን) ጠቅላላ ዋጋ 1.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. አንድ ተጫራች በጨረታው የተካተቱ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉ የኢንሹራንስ ዋስትና (አርቦን) መጠን ካልሞላ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

10. በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ድርጅት አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል፡፡

11. ጨረታውን የተጋበዙ ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻው ቀን ሳይደርስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ከመለሱ ጨረታውን መክፈት ይቻላል፡፡

12.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582201453 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ

ባህርዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Bid opening: 2026-09-01 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ
  • Bid bond: 1.5%
  • Published on: Be'kur (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T07:09:59.000Z
← Back to all tenders