Stationery
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ቁጥር ጨ-1/0248/2019
የቋሚ እና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የመኪና ጥገና እና ኢንሹራንስ አገት ግዥ አገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸዉን የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣
- የመኪና ጎማዎች፣ የስፖርት ትጥቆች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ አገት፣
- የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ እና ፈርኒቸርና የፈርኒቸር ዉጤቶች
- እንዲሁም የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥን በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡-
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፤
1. አሸናፊዉ ድርጅት አቅርቦቱን የመጫኛ፣ የማዉረጃና የማጓጉዋዣ ወጭ ሸፍኖ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች ንብረት ማከማቻ መጋዝን የሚያቀርብ እና የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎቱን በሠቆጣ ከተማ መስጠት የሚችል መሆኑን ሊገነዘብ ይገባል።
2. ከሚወዳደሩበት የአቅርቦት ወይንም የአገልግሎት ግዥ ጋር የተዛመደ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer identification Number) ያላቸዉ እና የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፣
6. የሚገዙትን እቃ እና አገልግሎት አይነት ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት⁄ምድብ የማይመለስ ብር 300/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፣
8.ተጫራቾች ጨረታዉ በሎት መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ምድብ ማለትም ለጽህፈት መሣሪያ = 187,553 ብር፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች = 377,871 ብር፣ ለጽዳት ዕቃዎች – 74,757 ብር፣ ለቆዳ ዉጤቶች = 113,897 ብር፣ የተዘጋጁ ልብሶች= 278,813 ብር፣ ፈርኒቸርና የፈርኒቸር ዉጤቶች = 92250፣ ለስፖርት ትጥቆች = 69277 ብር፣ ለከባድ ማሽን ጥገና አገ/ት - 50,000 ብር ለቀላል ተሸከርካሪ ጥገና= 70,000 ብር፣ ለከባድ ማሽን መለዋዎጫ = 150,000 ብር፣ ለREVO, Kun-25 እና Nissan ZN1033UBX ቀላል ተሸከርካሪ መለዋዎጫ = 50,000 ብር ለ1HZ-79/78/new,1HZ-105,1HZ-76,1HZ-79/old ቀላል ተሽከርካሪ መለዋዎጫ = 150,000 ብር፣ ለ3L-166 ቀላል ተሸከርካሪ መለዋዎጫ - 10,000 ብር፣ ለኢንሹራንስ አገ/ት = 120,000 ብር በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንከ ዋስትና ደብዳቤ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸዉ፣
9. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታዉ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስር ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ስአት ሠነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናዉን በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ርቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ አንደኛዉ ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
10. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዋኸ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ ርቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታዉ በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጥዋቱ 3፡30 ይከፈታል፣ ሆኖም ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀንና ሰአት ከመንግሰት የስራ ቀን ዉጭ ከሆነ በተመሣሣይ ሰአት በሚቀጥለዉ የመንግስት የስራ ቀን ይከፈታል።
11. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ሲሞሉ በነጠላ ዋጋዉም ሆነ በጠቅላላ ዋጋዉ ስርዝ ድልዝ ካደረጉ፣ በጨረታ መክፈቻዉ ወቅት የተነበበዉ ዋጋና የተሰራዉ የሂሳብ ስሌት ከሶስት በመቶ በላይ ልዩነት ካለዉ ወይንም ከሶስት በመቶ በታች ልዩነት ኑሮት የሂሳብ ማስተካከያ ካልተቀበሉ ወይንም ከገበያ ጥናቱ እና ከአንድ እስከ ሶስት ከወጡ አሸናፊ ድርጅቶች ከሚወሰደዉ ዋጋ ሲነጻጸር ተጫራቹ የሞላዉ ዋጋ ከአስር በመቶ በላይ ከተጋነነ ከጨረታዉ ዉጭ ይደረጋል።
12. ተጫራቾች ከገበያ ጥናቱ እና ከአንድ እስከ ሶስት ከወጡ አሸናፊ ድርጅቶች ከሚወሰድ ዋጋ ሲነጻጸር ተጫራቹ የሞላዉ ዋጋ ከሰላሳ በመቶ በታች የተሰበረ ከሆነ ለእያንዳንዱ የተሰበረ ዋጋ ሁለት በመቶ ከሚያስይዘዉ የዉል ማስከበሪያ በመጨመር የሚያስይዝና የቅድመ ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
13. መምሪያዉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ይህም ሲባል ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፣
14. ተጫራቾች ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይንም
በስልክ ቁጥር 033 440 1230/0249/0062 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-11-02
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-11-02 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Wag Himra Nationality Administration Finance and Economic Cooperative Command
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 300.00 (ሦስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
- Posted at: 2026-10-23T09:33:48.000Z
- Source: Qelal Tenders