Accounting and Auditing, Accounting System Design

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሴ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት አወዳድሮ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር CEDCSE/ NO 05/2018

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሴ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት አወዳድሮ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ፡-

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ፈቃዳቸውንና ምዝገባ ሰርተፍኬታቸውን ለ2018 ዓ.ም ያሳደሱ፤ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘረውን እያንዳንዱን ዋጋ ሞልተዉ / ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ፋይናንሻል ኦርጂናል ዶክመንት አንድ እና ፍይናሻያል ኮፒ ሁለት ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት አንድ እና ቴክኒካል ኮፒ ሁለት ለየብቻ በማድረግ እና በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በቀኑ 8፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ቴክኒካል ዶክመንት ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ በነፃ ከድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።

7. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 12 81 81 02 / 09 55 44 52 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡።

የድርጅቱ አድራሻ ሆሳዕና ከተማ ወደ ወልቂጤ መውጫ መንገድ ካቶሊክ ት/ቤት ጎን ላይ

ሆሳዕና ኢትዮጵያ

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-04 15:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በቀኑ በ9፡00 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Central Ethiopia Design and Construction Supervision Organization
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T11:57:39.000Z
← Back to all tenders