House and Building Foreclosure

ለመኖሪያ እና ለደርጅት የሚውል ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አቶ አብዱልፈታ በድሩ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ዶ/ር ሻወል ኃይለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/284257 በ18/7/2015 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/335404 በ18/07/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ በቀድሞው ወረዳ 23 ቀበሌ 15 በአሁኑ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ የካ/ቁ/03/32/6877/9970/01 የሆነ በ1258 ካ/ሜ ይዞታ ላይ ያረፈውን ቤት በቁጥር የካ/ቁ/03/32/6877/9970/01 በአቶ ሻወል ኃይሉ ግዛው ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 1258 ካ/ሜ ቤቱን/ቦታው/61 ካ/ሜ የሰፈር መንገድ የሚነካው ቤቱ ቦታው በካርታቸው መሰረት ለመኖሪያና ለደርጅት የሚውል የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 43,727,768 (አርባ ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የካፒታል ጌን ታክስን የሚከፍለው ሻጭ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለተ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻስን፡፡

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-29
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-29 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T09:14:15.000Z
← Back to all tenders