Building Construction

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ለኢኮኖሚ ክላስተር ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ G+3 ሕንፃ ግንባታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ለኢኮኖሚ ክላስተር ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ G+3 ሕንፃ ግንባታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ከታች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚታሟሱ ተጫራቾች አንዲትወዳደሩ እንጋብዛለን።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ያላት

2. የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው ያላት

3. ከግብር ሰብሳቢ መስርያ ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

4 የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር TIN/ ያለው/ያላት፤

5. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች

6. የታደሰ የሙያ ፈቃድ GC ወይም BC ከደረጃ (1-5) ማቅረብ የሚችል/የምትችል።

7. መልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል።

8. የግንባታ ቦታ የጎበኙበት ደብዳቤ ከአሰሪው መ/ቤት ማቅረብ የሚችል የምትችል።

9. የአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ወስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞው ማቅረብ አለባቸው።

10. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸዉ የብር መጠን ሲፒኦ /CPO/ በቼክ በመሎ ኮዛ ወረዳ ፈ/ጽ/ቤት ስም አሰርተው ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረትየባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነድ ጋር አንድ ላይ ማስገባት ይኖርበታል።

11. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ /500/ ብር አምስት መቶ ብር በመሎ ኮዛ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር-8 መግዛት ይኖርበታል።

12. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የግንባታ ስራው የመወዳደሪያ ሀሳብ ደጋፍ ሰነዶች በግልጽና በጥራት የሚታይ እና የሚነበብ መሆን አለባቸው፤ ይህም የሚሆነው ከላይ በተገለጸው መሰረት ሆኖ ከተገለጹት ጉዳዮችና ሁኔታዎች ጋር የተጣጣመና ተቀባይነት ያላቸው መሆን አለባቸው የማይነበብ እና የማይታዩ መረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

13. ተጫራቾች ከላይ ከ1-12 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል።

14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ21ኛው ቀን 8፡30 ታሽጎ በ21ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ

* መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

* ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 0910409544 ይደውሉ።

መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-15 15:00
  • Bid opening (note): ጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Melo Koza Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T09:26:57.000Z
← Back to all tenders