Construction Machinery

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን የበቾ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 2019 ዓ.ም በጀት ዘመን ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ማሽኖች ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን የበቾ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 2019 ዓ.ም በጀት ዘመን ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ማሽኖች ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

        የእቃዉ አይነት

  1. የመንገድ ስራ ማሽኖች ኪራይ

በጨረታዉ ለማሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠባቅባቸዋል

1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለዉ እና የዘመኑን (2019)ዓመት ግብር መክፈሉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

2. የVAT እና TIN ተመዝጋቢ መሆኑን ማቅረብ የሚችሉ ፣ የVAT ዲጂታል or ርስት ያለው እና TOT መክፈል የሚችል::

3. በመንግስት ግዢ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ ፤ የ 1 አመት ስራ ልምድ ያለዉ እና ከሰራበት ቦታ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።

4. ከወረዳው ጋር በመግባባት የስራ በግልም ሆነ በማህበር ተጣልቶ ያልተከሰስ እና ከበቾ ወረዳ መንገድ እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት ሁሉም ተጫራች የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የስራ ቦታ 1 ሌቃ ደምቦ ክላሰተር 2 በቾ ክላስተር ይህ እንዳለ ሁኖ አንድ ተጫራች ከአንድ ክላስተር በላይ መወዳደር አይችልም፡፡

6. የጨረታ ማስከበሪያ በተወዳደሩበት የጨረታዉ ዓይነት 100,000 ብር በባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡

7. ተጫራቾች ጨረታዉ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታዉን ሰነድ ከበቾ ወረዳ ገ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት በብር 500 ከቢሮ ቁጥር 11 መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ዋጋ ፣ የሰዓት፤ የቀን፤ ወይም የቢያጆ ሲሞሉ በማያሻማ ፅሑፍና የድርጅቱ ማህተም የኃላፊው፣ ፊርማ በሁሉም ገፅ ላይ በጥንቃቄ ተደርጎ ይህን ሰነድና ለዉድድር የሚያበቁ ማስረጃዎችን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. የጨረታዉ መክፈቻ ቀን ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ሲሆን በቅደም ተከተል 3፡00 ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን የጨረታዉ ሰነድ ማስገቢያ ሰዓት ሲሆን በ4፡00 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ካልተገኙም ጨረታዉ ይከፈታል።

10, 16ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል።

11. ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለዉና የብርና የሣንቲም አፃፃፍ አሻሚና የማይነበብ ከሆነ የተወዳዳሪዉ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡

12. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ስራቸዉ አፈጻፀም ስምምንት እንዲሆን ያሸነፈበት ጨረታ 10% በባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ /በህግ በተቀመጠ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

13. አሸናፊ ተጫራቾች ማሽኑን እስከ በቾ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት እና ስራ ቦታ/ሳይት⁄ ማስገባትና ከአንዱ ቦታ ሳይት/ ወደ ሌላ ቦታ /ሳይት/ ስራ የሚሰራበት ቦታ (site) ማቅረብ ማንቀሳቀስ, የሚችል

14. የማሽኑ የማስጫኛ እና ማውረጃ በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

15. አሸናፊ ተጫራቾች የስምምነት ውል ጨረታውን ባሸነፉ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀን መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡

16. አሸናፊ ተጫራቾች ማሽኑን በፈጸሙት ስምምነት መሠረት ካላቀረቡ ለስራቸዉ አፈጻፀም ያስያዙት 10% ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

17. ከላይ የተዘረዘሩት ማሽኖች እንደአስፈላጊነቱ ለስራ በሚፈለግበት ሰዓት ማሽኑን ሳይት ማስገባት የሚችል፡፡

18. ተጫራቾች ካቀረቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የተሻለ ዋጋ [List bider/ የማሽኑ አጠቃላይ ድምር ባቀረበዉ ዋጋ አሸናፊ ይሆናል

19. ተጫራቾች መብትና ግዴታዉን አዉቆ መዉጣት የሚችል መሆን አለበት፡፡

20.ጽ/ቤቱ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

21. ይህ ሰነድ የጨረታዉ አካል ነዉ።

22. ለበለጠ፡ መረጃ፡ በሞባይል ፡ቁጥር 0952359560

በኢሉባቦር ዞን የበቾ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታዉ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ሲሆን በቅደም ተከተል 3፡00
  • Bid opening: 2026-09-07 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታዉ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ሲሆን በቅደም ተከተል 4፡00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Illubabor Zone Becho Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T10:02:34.000Z
← Back to all tenders