Industrial Machinery Provision and Installation
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት የካፒታል ዕቃዎችን በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የድርድር ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት አሰጣጥ ለዮሴፍ እና ሀይሉ የልብስ ስፌት ሽርክና ማኅበር በኪራይ አስተላልፎለት የነበረው ዘመናዊ የልብስ ስፌት እና የጥልፍ ማሽነሪዎች ተከራዩ በካፒታል ዕቃዱቤ ግዥና ኪራይ ውሉ መሰረት የሚጠበቅበትን የማሸን ኪራይ ክፍያ በወቅቱ መከፈል ባለመቻሉ ባንኩ በካፒታል ዕቃ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/98 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 807/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የካፒታል ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ መልሶ በመረከብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የካፒታል ዕቃዎች በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ
|
በድርድር ሽያጭ የሚሸጠው የሚከራየው ንብረት ሁኔታ |
ብዛት
|
ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ |
የድርድር ሽያጭ ጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) |
የጨረታው ዓይነትና ደረጃ
|
የድርድር ሽያጭ ጨረታ የሚካሄድበት ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት |
|
|
የካፒታል ዕቃዎች ዝርዝር |
ዓይነት |
||||||
|
1 |
2 Needle,4 Thread Over Lock Machine Full Set |
Kansai
|
2 |
ጎንደር ከተማ አስተዳደር ፣ ማራኪ ክ/ከተማ ፣ ቀበሌ 18 ከሚገኘው የመንግስት ሸድ ውስጥ
|
8,516,045.93
|
የመጀመሪያ የድርድር ጨረታ
|
ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በጎንደር ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሚገኘው ቢሮ
|
|
2 |
Embroidery Machine (4 Heads) Full Set |
Tajima
|
1 |
||||
|
3 |
Tread Trimmer Machine |
Unison |
1 |
||||
|
4 |
Richpeace Pure Chenille Embroidery Machine (2 Heads) Full Set |
Richpeace |
2 |
||||
|
5 |
Upper and Lower Integrated Feed Pleating Lockstitch Machine |
Richpeace |
7 |
||||
|
6 |
Computer Control High Speed Straight Button Hole Sewing Machine |
Richpeace |
1 |
||||
|
7 |
Direct Drive Nailing Machine/button sewing |
Richpeace |
1 |
||||
|
8 |
Iron Boiler Machine |
Richpeace |
1 |
||||
የድርድር ሽያጩ ዝርዝር መመሪያ፡-
1. ከላይ የተመለከቱትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰቦች፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የሚገዛበትን ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በማዘጋጀት በዲስትሪክቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት የሚገዙበትን ዋጋ እና የግዥ ሁኔታ በመግለጽ ለዚሁ በተዘጋጀ ፖስታ ውስጥ በማሸግ እና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 03 ቀን 208 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ዲስትሪክቱ ጽ/ቤት በማቅረብ መደራደር ይቻላል፡፡
2. የድርድር ሽያጭ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፤
3. የጨረታው አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ተመሳሳይ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠበቁ ማናቸውንም ቀረጥና ሌሎች ክፍያዎች በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
4 አሸናፊው ተጫራጭ በተደራደሩበት ባቀረቡት የድርድር ዋጋ ላይ 15% Vፐ/ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡
5.ባንኩ አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ዋጋ ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መክፈል የሚኖርበት ሲሆን ገንዘቡን በተጠቀሰው ቀን ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ባንኩ የድርድር ጨረታ ሂደቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
6.በድርድር ጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በባንኩ ማህተም ተረጋግጦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
7.አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ ቢያንስ የማሸኑን ጠቅላላ ዋጋ 20 (ሃያ በመቶ) በቅድሚያ በመክፈል በ15 ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟለት የማሽነሪ ኪራይ የዱቤ ግዥ ውል መፈረም ይኖርበታል ፡፡ ነገር ግን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡
8.ንብረቶችን ከጨረታ ቀን በፊት በአካል ማየት ወይም መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ ከባንኩ ጋር ፕሮግራም መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ለማንኛውም ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ጎንደር ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05822022// 0582110184 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-09 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 20%
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T10:33:28.000Z