Machinery and Equipment

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት ሶስት አርቲኩሌትድ ትራክተር ኪራይ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች መግዛት ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ዙር የመጣ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- LP/OT/002/OKSF1&3/2018

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት ሶስት አርቲኩሌትድ ትራክተር ኪራይ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

ግዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)

አድራሻ፡-ኮልፌ ቀራኒዮ፣

ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ

በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞርያ / ቶታል ገባ ብሎ

የፌድራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ

ሕ-B ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ።

ስልክ ቁጥር (አድራሻ)+251-96 344 2882/+251-91 617 0834

አዲስ አበባ

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሶስት አርቲኩሌትድ ትራክተር ኪራይ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሽገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 29/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 29/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

5. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።

5. የጨረታው ማስከበርያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ60 ቀናት ነው።

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-04 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T08:34:26.000Z
← Back to all tenders