House and Building Sale
የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ወ/ሮ ሳባ ሰለሞን እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ እመቤት መታፈሪያ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/142406 በ25/02/2017ዓ/ም እና በኮ/ መ/ቁ/146773 በ08/05/2017ዓ/ም በዋለውችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 253 የካርታ ቁጥር ወ 05/ወዝ01/587/14438/.0 በሴሪያል ቁጥር 019384 በወ/ሮ ድንቅነሽ ተክሎ እና በአቶ መታፈሪያ በላቸው ስም የተመዘገበ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን 157.44 ካ/ሜ ይዞታው በፕሮፖርሽን ወይንም የጋራ ግቢ ነው ቦታው የሰፈር መንገድ 20 ካ/ሜ ይነካዋል። የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,646,510 ( አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ አስር ብር ) የጥራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ሱት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ cPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ/ጽ/ቤት ስም cPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሱ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-09-30 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Court Judicial Procedure Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T10:45:53.000Z