House and Building Sale

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ የቦታው ስፋት 201.72 ካ.ሜ የሆነ መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

 የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼  (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማስራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
  2. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  3. ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  4. የጨረታው አሸናፊ ከሚገዙት ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ የሊዝ ክፍያ፣ ግብር እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎችን ገዢ ይከፍላሉ። በተጨማሪ ከንብረቱ ጋር የሚገናኝ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ ገዢ ይከፍላል።
  5. ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል።
  6. የጨረታ ቦታ በአቢሲንያ ባንክ ጅማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት 5ኛ ፎቅ በዲስትሪክቱ አደራሽ ውስጥ ነው።
  7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-211-3304 /047-211-3312/ ጅማ ዲስትሪክት በመደወል መጠየቅ ይቻላል፤
  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማናቸውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

..

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና .

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታው ሰዓት

የንብረቱ አይነትና አገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.ሜ

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

የጨረታው ማስታወቂያ የወጣበት ጊዜ

1

አቶ መሀመድ ሁሴን

ተበዳሪው

 

ጅማ ከተማ፣ ጊንጆ ቀበሌ

3,370,713

 

መስከረም 28 ቀን 2019 ..

4:00 -5:00

 

5:00-5:30

 

መኖሪያ ቤት

 

201.72 ካ.ሜ

 

22117937

 

ለሁለተኛ

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-10-08 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T11:51:07.000Z
← Back to all tenders