House and Building Sale
ፀደይ ባንክ አ.ማ ሼድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
House and Building SaleSales, Disposals and ForeclosureHouse and Building Foreclosure
Addis Ababa
More tags
Description
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ አዲሱ ጌትነት ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉንና ዝርዝር ሁኔታዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጸዉን ሸድ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የንብረቱ መገኛ፤ደረጃና ካርታ ቁጥር |
የጨረታዉ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
አቶ አዲሱ ጌትነት |
አንዳሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ግንቦት 20 ክ/ከ ካርታ ቁጥር ባህኢፓ /0083/09 ስፋቱ 7000 ካ.ሜ |
73,192,563.45
|
በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።
- የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር 73,192,563.45 (ሰባ ሶስት ሚሊዮን አንድ ዘጠና ሁለት ሺህ አምስት መቶ ስድሳ ሶስት ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም) ብቻ የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።
- በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጫረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸመል።
- የጨረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከሸዱ ጋር የተያያዙ ማንኛዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ወጭዎችን ገዢ ይከፍላል። ማንኛዉም ዉዝፍ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ዉል እንዲዋዋል ይደረጋል።
- ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
- ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር አሰራርና መመሪያ (መመዘኛዎች) ለሚያሟላና ፍላጎት ላለዉ ተጫራች ባሸነፈበት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰላ ባንኩ እስከ 30% ( ሰላሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ጨረታዉ የሚካሄደዉ መስከረም 20/2019 ዓ ም ከጠዋቱ 3.00 እስከ 6.00 ሰዓት በባህር ዳር ከተማ ጣና ክ/ከተማ ቀበሌ 16 ልዩ ቦታዉ ፀደይ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ከድሮዉ አልካን ጎን ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251 11 558 2978 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-30 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Published on: Reporter (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T13:44:37.000Z