House and Building Sale

የቦታ ስፋት 152 ካ.ሜ የሆነ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

 የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ሄኖክ ንጋቱ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ብርቄ ወመድህን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/325844 በ1/5/2016ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/330784 በ26/06/2016ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ በቀድሞ ወረዳ 04 በአሁኑ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 173 የሆነ መኖሪያ ቤት የይዞታ መለያ ቁጥር AA000030400359 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 152 ካ/ሜ ይዞታው በሰሜን 6 ሜትር ስፋት የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሚያዋስነው ሲሆን መንገዱ ተግባራዊ ሲደረግ 28.23 ካ/ሜ ስፋት ያለው ቦታ የሚቀነስ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 8,273,896 ( ስምንት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-10-01 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T07:34:06.000Z
← Back to all tenders