Water Pipes and Fittings

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

  •  ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ማናቸውም ህጋዊ እውቅና ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን አረርቲ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የምትጫረቱበትን ዋጋ ሰነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንድታቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15/አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው /በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታው ሲቀርቡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሰነዶች፡-

1ኛ. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ

2ኛ. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት

3ኛ. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት

4ኛ. ለተጨማሪ ታክስ ግብር ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ማስረጃ

5ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒ ማስያዝ አለባቸው

6ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ማስያዝ አለባቸው፡፡

7ኛ. ተጫራቾች የጫረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ/0222230144 ሞባይል 0922659065

የአረርቲ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው /በአስራ ስድስተኛው/ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው /በአስራ ስድስተኛው/ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Arerti Wereda Water and Sewerge Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T08:05:34.000Z
← Back to all tenders