Accounting and Auditing, Accounting System Design

ዘ ዩዝ ፕሪንት (The Youth Print) የ2018 ዓ.ም እ.ኢ.አ የአንድ ዓመት ሂሳብ በታወቀ B እና ከዚያ በላይ ደረጃ ባለው ፐብሊክ ኦዲት ድርጅት ለማስመርመር ይፈልጋል

Description

የኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ዘ ዩዝ ፕሪንት (The Youth Print) በኢትዮጵያ ውስጥ የተመዘገበ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ግቦች ላይ እየሠራ ይገኛል፡፡ በተባበሩትመንግሥታት ድርጅት 2030 ዘላቂ የልማት ግቦች (SDGs) እና በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ለማሳካት አዳዲስ የወጣቶች ሃሳቦችን እና ፕሮጀክቶችን በትምህርት፣ በምርምር፣ በፖሊሲ ትንተና፣ ትርጉም ያለው ውይይት እና ዓለም አቀፍ ትብብርን በመፍጠር ላይእንዲሁም በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ የ2018 ዓ.ም እኢአ የአንድ ዓመት ሂሳብ በታወቀ B እና ከዚያ በላይ ደረጃ ባለው ፐብሊክ ኦዲት ድርጅት ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ሥራውን ለማከናወን የሚጠይቁትን የገንዘብ መጠንናሥራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ በመጥቀስ፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ከታች በተገለጸው አድራሻ መሠረት በፖስታ አሽገው በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡

የኦዲት ድርጅቶቹ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

ሀ. ኦዲተሩ የሙያ ማረጋገጫ ያለው መሆኑ፣

ለ. የንግድ ፈቃድ ያለው መሆኑ፣

ሐ. የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆኑ፣

መ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው መሆኑ፣

ሠ. ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ያለው መሆኑ፡፡

አድራሻ፡- ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 H.NO/Gol.

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0947396499 / 093611495 መደወል ይቻላል፡፡

Email: [email protected]  [email protected] 

ዘ ዩዝ ፕሪንት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-09-03 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: The Youth Print
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T08:56:16.000Z
← Back to all tenders