Service

አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ማሰራት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በሦስተኛ ወገን የሚፈጸም የጥበቃ አገልገሎት ግዥ

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ግዥ

የጨረታ ቁጥር 002/2019

አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ኢንዱስትሪያችን በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚገኘው ኢንዱስትሪ የጥበቃ አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

1. የ2018/2019 በጀት አመት ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የጊዜ ገደቡ ያላለፈበት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (Tax Clearance)፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት(VAT)፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (PPA Website supplier list) ማቅረብ አለባቸው::

2 የግል የጥበቃ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከፖሊስ ማቅረብ የሚችል፡፡

3. ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የጥበቃ አገልግሎት የሰጠ እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤዎች የሚያቀርብ፡፡

5. በጥበቃ ጉድለት ለሚፈጠር አደጋ ዋስትና የሚወስድ (የሚሰጥ) ኢንሹራንስ ያለው፡፡

6. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 በመምጣት እንድታስገቡ ተደርጎ ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ሆኖ በእለቱ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡

7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ ስም ሒሳብ ቁጥር 1000014630906 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ- አርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት 7፡00-11፡00 ሰዓት ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ በመቅረብ ሰነዱን ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡

8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (አምሳ ሺ ብር) በCPO ወይም bank guarantee ወይም Cash ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

9. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡

10. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከአ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ሸገር ከተማ የቀድሞ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 0981 641 979 / 0912 088 636

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 14:15
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8:15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Engineering Group Akakai Basic Metals Industry
  • Buyer address: ከአ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ገላን ከተማ ሳይደርስ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T09:00:02.000Z
← Back to all tenders