Industrial Machinery Provision and Installation
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎችን ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ እጅ በእጅ በካሽ ወይም በከፊል ዱቤ ለመሸጥ/ ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የኢትዮዽያ ልማት ባንክ
ሀዋሳ ዲስትሪክት የክፍት ድርድር ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪከት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ ዘሪሁን ሙላቱ የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሠረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ሽያጭ እጅ በእጅ በካሽ ወይም በከፊል ዱቤ ለመሸጥ ለማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ. |
የንብረቱ ዝርዝር |
ብዛት በቁጥር |
የድርድሩ መነሻ ዋጋ |
የንብረቱ ሁኔታ
|
የድርድሩ ሁኔታ |
ድርድሩ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Baking Rotary Oven with Bumer Brand: ALTUNTOP, Model: ATDF- 250, Trolley capacity 16shelves, Origin: Turkey |
1 |
9,792,345.08
|
አዲስ
|
ክፍት ድርድር |
ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የባንኩ ሥራ ቀንና ሰዓት
|
|
2 |
Mixer Brand: ALTUNTOP, Model: ATSM120, Flour capacity - 75Kg, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
3 |
Dough Divider Brand: ALTUNTOP, Model ATK60T, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
4 |
Dough Moulder Machine Brand: ALTUNTOP, Model: ATF2, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
5 |
Proofer with Steam Generator Brand: ALTUNTOP, Model: ATPC, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
6 |
Trolley with 16 trays Brand: ALTUNTOP Pan Dimension - 80x100 Number of pans per trolley - 16 Material Aluminium |
4 |
||||
|
7 |
Bread Slicer Brand: ALTUNTOP, Model: ATED, Origin: Turkey |
1 |
||||
|
8 |
Sound Proof Generator Brand: AKSA, Model: AP33, Rated power: 30KVA |
1 |
የክፍት ድርድር ጨረታው መመሪያ
1. በድርድር ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተደራዳሪ የታደሰ መታወቂያ ኮፒና የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማመልከቻ፣ የድርድሩን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር 1,958,469.02 አንድ ሚሊዮን፤ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስምንት ሺ፣ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከ0.2 ሳንቲም/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የባንኩ ሥራ ቀንና ሰዓት የኢት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪከት ሎን ዎርከ አውት ዲቭዥን ቢሮ ማመልከቻውን ይዞ መቅረብ ይችላል።
2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፣መናኸሪያ ከ ከተማ፣ጉዊ ቀበሌ ባንኩ ከሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ነው።
3.ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች።
3.1. የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ የታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
3.2. ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ያስፈልጋል ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን የጉምሩክ ቀረጥና ታከለ መክፈል ግዴታ አለበት።
4. የድርድር ጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ የድርድር ጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል።
5. ንብረቱን በባንኩ ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል።
6. የድርድር ጨረታው አሸናፊ፣ አሸናፊ ሆኖ አስፈላጊውን ሂደት ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ወጪዎችን ማለትም የመጠሊያ ኪራይ፣ የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት።
7. የካፒታል ዕቃው ካለበት መጋዘን ወደ ሚፈልግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፣ የጉዞ ኢንሹራንስ ፣መትከያ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ተከራይ ይሸፍናል።
8. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪከት ሎን ዎርክ አውት ዲቭዥንን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
9.ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በድርድር ጨረታው አይገደድም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የባንኩ ሥራ ቀንና ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-30 12:00
- Bid opening (note): ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የባንኩ ሥራ ቀንና ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 20% ብር 1,958,469.02 አንድ ሚሊዮን፤ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስምንት ሺ፣ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከ0.2 ሳንቲም
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T09:00:13.000Z