House and Building Sale
ስፋቱ 339.55 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ ሐረገወይን ግርማ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አለማየሁ ግርማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/03001077 በ25/07/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/101186 በ15/4/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 05 ቀጠና 04 ሰፈር ኢትዮ ሴራሚክ የይዞታ መለያ ቁጥር AA000100500656 የሆነ ይዞታ ውስጥ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን ከግቢው የሚደርሳቸው ድርሻ 831 ካ/ሜ የሆነ አሁን በአካል ያለው 339.55 ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበት ሆኖ ቦታው የመንገድ ጥናት 143 ካ/ሜ ይነካዋል፡፡ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 27,774,994 (ሃያ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት) ሆኖ የትራዛከሽን ታከስ ገዥየሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉትአራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-10-02 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 26, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T10:52:13.000Z