Equipment and Accessories
በማዕከላዊ /ኢ/ከ/መንግስት የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማህረሰብ ቴሌቪዢን ለማስጀመር የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ እቃዎች ግዢን ለመፈጸም ተጫራቾችን ለማወዳር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 3/2018-2019
በማዕከላዊ /ኢ/ከ/መንግስት የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማህረሰብ ቴሌቪዢን ለማስጀመር የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ እቃዎች ግዢን ለመፈጸም ተጫራቾችን ለማወዳር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው
4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
5. የግዢው መጠነ ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፤ የአምራቹን ስም ፤ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጋር መያያዝ አለበት ፤
8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፣
9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንከ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
10. ተጨራቾች የተገለፀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር በጉ/ዞ/ገ/መምሪያ በመከፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር/10/ ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት አለባቸው ፤
12. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስና መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፤
13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
14. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-330-0112 ደውለው መጠየቅ ይቻላል
15. የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና ዕሁድ ወይንም፤የበአል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን የሚሸጋገር መሆኑ እንገልጻለን
ማሳሰቢያ ፦ ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ ተጫራቾች 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
በማዕከላዊ /ኢ/ክ/መንግሥት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Gurage Zone Finance Office
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T12:22:36.000Z