Generators
የአገው ግምጃ ቤት ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በድርጅቱ የውሃ መገኛ ቦታ ላይ የሚገኘውን ጀኔረተር በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአገው ግምጃ ቤት ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በድርጅቱ የውሃ መገኛ ቦታ ላይ የሚገኘውን ጀኔረተር በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ጨረታው ለማንኛውም ተጫራች ክፍት ነው፡፡
- የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩት ከጠቅላላ ዋጋ የማመለስ 5 በመቶ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅታችን ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱን አገው ግምጃ ቤት ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ ግዥና ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ መነሻ ዋጋ ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) ሲሆን ዝርዝር መግለጫው በሰነዱ ላይ ያለ በመሆኑ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም 11፡00 ድረስ በሥራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምር ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ህዝባዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን 8፡00 ታሽጎ 8፡15 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበትና ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ሙሉ ክፍያውን ዕቃ እስካለበት ቦታ ድረስ ዕቃውን መረከብ እና ክፍያ በባንክ ገቢ የተደረገውን ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀን ክፍያ ባይፈጽሙ የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ የሚጠቀም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ የሚለይበት ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ብቻ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 04 62 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአገው ግምጃ ቤት ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): በ16ኛው ቀን ህዝባዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-08 14:15
- Bid opening (note): በ16ኛው ቀን ህዝባዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን 8፡15 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የአገው ግምጃ ቤት ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
- Bid bond: 5 በመቶ/ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር)
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Be'kur (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-27T07:38:00.000Z