House and Building Foreclosure

ፀደይ ባንክ (አ.ማ.) መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ (አ.ማ) ዘንገና ቅርንጫፍ ለአቶ አለኸኝ ጥላሁን እና ለወ/ሮ ማሪቱ መንግስቴ እና ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ቅርንጫፍ ለአቶ አለ አድማስ እና ወ/ሮ ብዙአየሁ ገነት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሰንጠረዥ ከዚህ በታች የተገለፁ መያዣዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪ ስም

የካርታ ቁጥር

ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

የቦታ ስፋት በካ/

የንብረቱ አይነት አገልግሎት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

የጨረታ ቀንና ሰዓት

ጨረታ የወጣው

አለኸኝ ጥላሁን እና ማሪቱ መንግስቴ

አለኸኝ ጥላሁን እና ማሪቱ መንግስቴ

108/09

እንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ

200 /

መኖሪያ

2,193,213.81

መስከረም 15/2019 /300-600

ለመጀመሪያ ጊዜ

አለ አድማስ እና ብዙአየሁ ገነት

አለ አድማስ እና ብዙአየሁ ገነት እና እመቤት አወቀ

625//4382 እና 402//822

ዳንግላ ከተማ 04 ቀበሌ እና 05

150 /እና 105 /

መኖሪያ

952,334.72 እና 1,265,703.28

መስከረም 15/2019 /300-600

ለመጀመሪያ ጊዜ

ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛውን (በጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቃላ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይከፍላሉ፡፡
  6. 6. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት ጨረታው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
  7. 7. የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  8. ጨረታ የሚካሄደው መስከረም 15/2019 ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 የተጫራቾች ምዝገባ ተካሂዶ ከረፋዱ 5፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በእንጅባራ ከተማ ፀደይ ባንክ እንጅባራ ዲስትሪክት ቢሮ ይካሄዳል፡፡
  9. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  10. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  11. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  12. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 227 07 08 /09 18 44 45 41 /09 18 80 27 26 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-25
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-09-25 09:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Be'kur (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-27T07:40:55.000Z
← Back to all tenders