House and Building Sale
የቦታው ስፋት 84 ካ.ሜ. የሆነ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ስምኦን ተክሌ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ዘመደ ወ/ስላሴ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 15464 በየካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 15464 በ24/2/2018ዓ.ም በኮ/መ/ቁ 15464 በ4/9/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር 3314 የካርታ ቁጥር 3/20/3/7/16-8/4/10785/01 የሆነ በቀን 27/11/2018ዓ.ም በተደረገው ክፍፍል በ “A” የሰየምነው የቦታ ስፋት 84 ካ.ሜ. ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,630,464 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰላሳ ሺህ አራት መቶ ስልሳ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ መሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-02 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
- Posted at: 2026-08-27T08:09:27.000Z