House and Building Sale

የቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ እንግዳ ወርቅ አባቡ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ትዕግስት አበበ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/98075 በ15//2017 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/03848 በ29/03/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/03848 በ22/1/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት

1ኛ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 666 የካርታ ቁጥር 6/67/370438/0ı በእነ አበባ ዘውዴ ደስታ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 546 ካ/ሜ ውስጥ መጋዘኑ ከውርስ ሀብት ውጭ የተባለው ቤት 72 ካ/ሜ ስለሆነ ከጠቅላላ ይዞታው ላይ 472 ካ/ሜ የሚደርስ ሲሆን ይዞታው በፕሮፖርሽን ሆኖ ከመጋዘኑ (ከውርስ ውጭ) ያለው ቤት 472 ካ/ሜ የሀፐነ ቤት እና የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 11,298,587 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ሰባት ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ/ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 15 የቤት ቁጥር አዲስ የይዞታ መለያ ቁጥር AA00008119545 በምስራቅ አበበ ዘውዴ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 72ካ/ሜ የቤቱ ስፋት 213.60 ካ/ሜ ቤት እና ይዞታ ይዞታው G+3 የሆነ ቤት ከይዞታቸው ላይ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 10 ካ/ሜ ያህል ይነካዋል። የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 6,852,360 (ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል የፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-06 14:30
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 29, 2026)
  • Posted at: 2026-08-29T07:48:52.000Z
← Back to all tenders