Products and Services

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በሀዋሳ እና በሆሳዕና በድርጅቱ መጋዘኖች ተከማችቶ የሚገኝ ከዘርነት የተረፈ ለምግብነት የሚውል ንፁህ የቦቆሎ እና ንጹህ የስንዴ እህል በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 012/ሽያጭ/18 ዓ.ም

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በሀዋሳ እና በሆሳዕና በድርጅቱ መጋዘኖች ተከማችቶ የሚገኝ ከዘርነት የተረፈ ለምግብነት የሚውል ንፁህ የቦቆሎ እና ንጹህ የስንዴ እህል በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡

  • ተጫራቾች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ በየሎት 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ / ሲሆን የሎት ብዛት እና የእህሉ መጠን በሚሸጥ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል። የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ/ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የስብሰባ አደራሽ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
  • የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጐ በእለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የስብሰባ አደራሽ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል።
  • ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በስልክ ቁጥር 046 220 1752/2285/2117
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ሀዋሳ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Southern Seeds Enterprise
  • Bid bond: በየሎት 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T07:57:54.000Z
← Back to all tenders