Accounting and Auditing, Accounting System Design

መሳለሚያ አካባቢ ነጋዴዎች አንድነት አክሲዮን ማህበር የኦዲት/የሂሳብ/ ምርመራ ጨረታ ማስደረግ ይፈልጋል

Description

የኦዲት/የሂሳብ/ ምርመራ ጨረታ

ድርጅታችን መሳለሚያ አካባቢ ነጋዴዎች አንድነት አክሲዮን ማህበር የንግድ ማዕከል ህንፃ ገንብቶ የንግድ ቤቶችን እና ፓርኪንግ በማከራየት የንግድ ስራውን የሚሰራ ድርጅት ነው::

የሂሳብ ምርመራ ዓይነት፡-

1. የ2018 ዓ.ም የገቢ እና የወጪ ሂሳቦችን በዝርዝር እና በተሟላ የኦዲት ምርመራ እንዲከናወንለት ነው:: ይኸውም ፋይናንሻል ሪፖርት ኦዲት እንዳልሆነ እያሳወቅን ምርመራ የሚካሄድባቸው፡-

  • የሰነድ እና ዶክመንት ማሟላትና ማረጋገጥ፤
  • በገቢ እና ወጪ ሂሳብ ክንዋኔው ያሉት የሂሳብ ጉድለት፣ ጥፋት፣ ስህተቶች፣ ግድፈቶች እና የሕግና መመሪያ መሰራቱን ማረጋገጥ፤
    የገቢ እና የወጪ ማከናወኛ ሰነድ መሟላትን ማረጋገጥ፤ 
  •  በኦዲቱ ወቅት ከኦዲቱ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ፋፈል እና ዶክመንቶች ለሂሳብ ምርመራው ካስፈለገ አስቀርቦ እንዲመረመር ማድረግ፤
  • ኦዲቱ ነፃ እና ገለልተኛ ሊሆን ይገባል፤
  • የስራ አመራሩ ለኦዲት ስራው ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ ተገቢውን ድጋፍ እና እገዛ ያደርጋል፤
  • የመጀመሪያ ድራፍት ሪፖርት ለማኔጅመንት ቀርቦ በኦዲት ባለሙያው አስተያየት ይሰጣል፤

2. የካፒታል ሂሳብ ኦዲት የአ/ማህበሩ አባላት መዋጮ እና ከዚህ ጋር የተያያዙትን ፋይል እና ሰነድ መመርመር የካፒታሎቹን ትክክለኛ መጠን ማረጋገጫ መስጠት

የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርት፡-

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት

3. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ

4. የስራ ልምድ እና የባለሙያ ፕሮፋል

5. ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል

6. የኦዲት መጠናቀቂያ ጊዜ ለተራ.ቁ 1 ኦዲት እስከ 20 ቀናት ለተራ ቁጥር 2 ኦዲት የሚጠይቀው ጊዜ ታይቶ በሚቀርበው በጋራ የሚወስን

7. በኦዲት የሚቀርበው መወዳደሪያ ዋጋ ለካፒታል ኦዲት እና ለተራ.ቁ 1 የ2018 ኦዲት ለየብቻ ተገልፆ ተጠቅሶ የሚቀርብ ነው፤

8. አ/ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ከወሰደ አይገደድም፤

የማቅረቢያ ጊዜ፡-

  • ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይቻላል::

ለጽ/ቤታችን የጨረታ ሰነድ በግንባር ለምታቀርቡ

አድራሻ፡- ከአውቶቢስ ተራ አለፍ ብሎ መሳለሚያ ከእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዝቅ ብሎ አማኑኤል ፀጋ ህንፃ በስተጀርባ ባለው የማህበሩ ህንፃ (ሆናልያት ሞል) 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402

ማሳሰቢያ

  • ማንኛውም መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-47-00-14/ 0999-14-88-48 መጠየቅ እና መረዳትይችላሉ::
  • በቴሌግራም ለመላክ በ0999-14-88-48

Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይቻላል
  • Bid opening: 2026-09-10 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mesalemia Area Traders Unity S.C.
  • Published on: Reporter (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T14:45:51.000Z
← Back to all tenders