Building Construction

በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በኦዳ ማዘጋጃ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የውሃ ታንክር ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019

በካፋ ዞን የጠሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በኦዳ ማዘጋጃ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የውሃ ታንክር ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

ሀ/ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባና የሥራ ፈቃድ

ለ /የቲን TIN/ምዝገባ ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ሰርተፍኬት

ሐ/ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት

መ/ ከ2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ለግንባታዎችም መልካም አፈፃጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችልና የግንባታውን ሥራ በገባው ውል መሠረት የሚያስረክብ

ሠ/ በግንባታው ወቅት በተደጋጋሚ ማስታወቂያ ያልወጣበት

ረ/ ተጫራቾች ግንባታ የሚገነባበት ከኦዳ ታዳጊ ማዘጋጃ የሳይት ምልከታ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው

ተጫራቾች ከሀ እስከ ረ የተጠቀሱትን የንግድ ፈቃድ የቫትና የግብር ከፋይነትን መለያ ቁጥር እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን የጨረታ ዶክመንት ሲገዙ ኦርጅናሉንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ የሠነድ ሽያጭ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 21 የሥራ ቀናት ጠሎ ወርዳ ፋይ/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ ር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ጠሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የሥራ ቀናት የጠሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ እና ንብ/አስ/ር በመቅረብ ለዚሁ ሥራ ለተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ግንባታዎች ፍቃዳቸው WWC/GC/ ደረጃ 7 እና ከ7 በላይ, አሸዋ 1ኛ ደረጃ መሆን አለበት”

በገቡበት ውል መሠረት ጊዜና ቀናትን ጠብቀው ሠርተው ማስረከብ የሚችል

የመሐንዲስ አስተያየት ተቀብሎ ለመስራትና በሚሠጠው አስተያየት ተገቢውን ሥራ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ

የጨረታው ሳጥን በ21ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ22ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ከጧቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ሂደት አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም።

ከዋጋ ጥናቱ ከ15% በታች በሆነ ዋጋ ጨረታ የሚያሸንፍ ተወዳደሪ ያለቅድመ ክፍያ ሥራ ይጀምራል። እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 20% የሚያሲይዝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በተደረገው የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ /Arithmetic Error የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡

የመክፈቻው ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ 0917757968/092422660//0917324456 ደውለው ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጠሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-24 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጧቱ በ3፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Kaffa Zone Tello Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T08:30:21.000Z
← Back to all tenders