Transportation Service
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር የፕሮጀክት ግንባታ ጽ/ቤት ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችሉ የትራንስፖርት ማህበሮችን ወይም ግለሰብ ባለንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድ/ዳ/አስ/የፕ/ግ/ጽ/ቤት/ግ/ጫ/0002/2019
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር የፕሮጀክት ግንባታ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የስራ ክፍሎች ለሠራተኞች ሰርቪስ እና በዘጠኙም ቀበሌዎች ባለሞያዎችን ይዞ በመዘዋር የመስክ የሳይት ስራዎችን አገልግሎት የሚሰጥ ደረጃ ሁለት የሆነ ሚኒባስ ተሸከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችሉ የትራንስፖርት ማህበሮችን ወይም ግለሰብ ባለንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የትራንስፖርት ማህበሮችን ወይም ግለሰብ ባለንብረቶችን ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
2.የታደሰ የቀበሌ /የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል፣
3.የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍከት ያለው፤
4.የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለው፤
5.በአቅራቢ ዝርዝር ላይ የተመዘገበ ሆኖ የምስክር ወረቀት ያለው፤
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 4,650.00(አራት ሺ ስድስት መቶ ሃምሳ ብር) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመወዳደሪያ ዋጋቸው ጋር አያይዘውና አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
7. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ሰነዱን በመግዛት እና የመጫረቻ ዋጋቸውን በመሙላት ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳዳር የፕሮጀክት ግንባታ ጽ/ቤት የግዢ ፋይናንስና የሰው ሀብት አስተዳደር ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
8. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4፡30 ላይ ይከፈታል ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቶች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገጸላቸውና ውል ከፈጸሙ በኃላ ወዲያውኑ ስራ መጀመር የኖርባቸዋል፤
10. የስራ ውሉ እንዲቋረጥ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ውሉ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም ድረስ ይቆያል፤
11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፤፤ ለተጨማሪ መረጃ 0935 648 866/0915 738 204
የድሬዳዋ አስተዳዳር የፕሮጀክት ግንባታ ጽ/ቤት
አድራሻ፤- የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 002
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-10 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: የድሬዳዋ አስተዳዳር የፕሮጀክት ግንባታ ጽ/ቤት
- Bid bond: 4,650.00(አራት ሺ ስድስት መቶ ሃምሳ ብር)
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ) ብር
- Published on: Melekite Dire (Aug 26, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T15:30:19.000Z