House and Building Sale
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 2ኛ ቤተሰብ ችሎት የቤት የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል
Description
የመ/ቁ 109221
ቀን 27/11/2018ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ መሀመድ አህመድ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አብዱልኪም ኡመር ሳዲቅ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 107774 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 01 አስተዳደር ክልል ውስጥ በፍርድ ባለዕዳ ስም ተመዝግ የሚገኝ የቤት ቁጥር A-402 የሆነ ቤትና ይዞታ በሃራጅ መነሻ ዋጋ ብር 973,886.51 /ዘጠኝ መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር 51/100/ በሆነ ዋጋ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡45 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡50 እስከ 5፡40 ባለው ጊዜ ይከናወናል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ የጨረታው መነሻ ዋጋ 1/4ኛ CPO በማስያዝ ወይም በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በሞዴል 85 ማቅረብ እና ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው፡፡ ቀሪውን 3/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 2ኛ ቤተሰብ ችሎት
Tender details
- Deadline: 2026-10-10
- Bid closing time: 10:50
- Bid opening: 2026-10-10 10:50
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Dire Dawa Federal First level Court
- Bid bond: 25%
- Published on: Melekite Dire (Aug 26, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T06:32:39.000Z