Insurance Service
የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለአሰሪዎችና ለሰራተኞች የመድህን ዋስትና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ኢንሹራንስ ድርጅቶች ለመግዛት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉን ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለ2010 በጀት ዓመት የአካባቢግልፅ ጨረታ መመሪያ 16/2018 መሰረት የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለአሰሪዎችና ለሰራተኞች የመድህን ዋስትና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ኢንሹራንስ ድርጅቶች ለመግዛት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉን ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. የዘመኑን ግብር ከፍለው፤ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ እና የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች በኮርፖሬሽኑ ስም የተሰራ ሲፒኦ ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል (Unconditional Bid bond guarantee) ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው:: አሸናፊው ከተለየና ውል ከተፈረመ በኋላ ላላሸነፉት ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ዝርዝር መግለጫ መሰረት በተገለፀው የአሰሪዎችና ለሰራተኞች የመድህን ዋስትና የአገልግሎት ግዥ የሚያቀርቡትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻልም፤ ካለ ግን ዋጋውን በሞላው አካል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ይከፈታል:: የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ
ማድረግ አይችሉም፡፡
8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ ማስታወቂያው ይገለፃል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058-222-1479 ወይም 0930111746 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን 8:00
- Bid opening: 2026-09-19 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን 8:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Water Works Corporation
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Be'kur (Aug 31, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T07:54:59.000Z