House and Building Sale

ዳሽን ባንክ አ.ማ. ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

የሐራጅ ቁጥር ዳባ/0034/26

ዳሽን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚከተሉትን ተበዳሪ ወይም አስያዥ ንብረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ ይሸጣል።

.

የተበዳሪው ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

የአስያዥ ስም

 

ለጨረታው የቀረበው ንብረትና የቦታው ስፋት

የጨረታው መነሻ ዋጋው (ብር)

የጨረታው የሚካሄድበት

ከተማ፣ /ከተማ፣ ወረዳ

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

ቀን

ሰዓት

1

መላኩ ታምሩ ግዛው

ልደታ

ተበዳሪው

 

ሸገር ከተማ ኮዬ ፈጨ /ከተማ

OR000070901103 4510001

 

 

41.96 .

1,924,492

ጥቅምት 03 ቀን 2019 .

4:00 -6:00

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(C.P.O) በዳሽን ባንክ አ.ማ. በማስራት በጨረታው ዕለት ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ይካሄዳል።

3. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈለው ግብር፣ ታክስ፣ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) እና ሌላ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ወጪዎችን ገዢው/አሸናፊው/ ይከፍላል።

4. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠዉ ተጫራች በጨረታዉ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰዉ ብቻ ነዉ።

5. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያሲያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

6. በጨረታው ላይ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፤ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።

7. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሠዓት 10 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።

8. ጨረታው ተጀምሮ በተቀመጠው ሰዓት ውስጥ ካልተጠንቀቀ ሊራዘም ይችላል።

9. ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች አብርሆት ቤተ መጽሀፍት አካባቢ በሚገኘዉ ዳሽን ባንክ (አ.ማ) ሰሜን አዲስ አበባ ቀጠና ብድር ማስመለስ ክፍል በስራ ሰአት በመገኘት ክፍሉ በሚያመቻቸዉ ፕሮግራም መሰረት ንብረቱን መጎብኘት ይቻላል።

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 170 4038 ወይም 011 170 4953 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዳሽን ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-10-13
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-10-13 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dashen Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T08:14:15.000Z
← Back to all tenders