Pumps, Motors and Compressors

የመቐለ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት የሚያገለግል ሙሉ ባለ ቡዙ ምዕራፍ ሴንትሪፍዩጋል ከመሬት በላይ የሚገጠሙ የውሃ ፓምፖች ከሞተር ጋር አቅርቦት (Procurement of Supply of complete multi-centrifugal Surface pumps with motor) ግዢ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ስለፈለገ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቶች ጥሪውን ያቀርባል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የመቐለ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት የሚያገለግል ሙሉ ባለ ቡዙ ምዕራፍ ሴንትሪፍዩጋል ከመሬት በላይ የሚገጠሙ የውሃ ፓምፖች ከሞተር ጋር አቅርቦት (Procurement of Supply of complete multi-centrifugal Surface pumps with motor) ግዢ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ስለፈለገ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቶች ጥሪውን ያቀርባል፡፡

1, የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድና የአቅራቢዎች መታወቅያ ፍቃድ ያላቸው

2, ቫት የተመዘገበና የመጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ ቲን ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ

3, የጨረታው ዶክሜንት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 2000 (ሁለት ሺህ) በመክፈል መቐለ ውሃ አግልግሎት ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታው ዶክሜንት ከደጋፊ ስራ ሂደት ግዢ ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር G1-02 መግዛት ይችላሉ፡፡ 

4, ጨረታ ዶክሜንቱ ማስገባት የሚቻለው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 2019 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ወደ ጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይችላሉ።

5. ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15ኛው ቀን 2019 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እሁድ ወይ ህዝባዊ በአል ከሆነ ደግሞ ቀጥሎ ባለው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራች ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሁሉም ተጫራቶች የሙሉ ባለ ብዙ ምዕራፍ ሴንትሪፍዩጋል ከመሬት በላይ የሚገጠሙ የውሃ ፓምፖች ከሞተር ጋር አቅርቦት (Procurement of Supply of complete multi centrifugal Surface pumps with motor)ግዢ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበርያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክረዲት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል

6. ተጫራቹ ነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪም በጨረታ ዶክሜንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው።

7, በዶክሜንቱ ከተሰጠው ስፔስፍኬሽን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።

8. የጨረታው አሸናፊ ውል ማስከበርያ ካሸነፈው ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ዋስትና የውል ማስከበርያ (Performance bond guarantee) 10% ማስያዝ የሚችልና በ3 ቀን ውስጥ ውል አስሮ በዶክሜንቱ በተጠቀሰው ቀን ንብረቱን ማስገባት የሚችል

9, በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛበት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግስት ግዢ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ወደ ክልሉ ፋይናንስና ፕላን ቢሮ ደብዳቤ እንደምንፅፍ

10. ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣውን የጨረታ ዶክሜንት ተቀባይነት የለውም።

11. ጨረታ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ ለ45(አርባ አምስት) ቀን ሙሉ ባለ ብዙ ምዕራፍ ሴንትሪፍዩጋል ከመሬት በላይ የሚገጠሙ የውሃ ፓምፖች ከሞተር ጋር APCO (Procurement of Supply of complete multi-centrifugal Surface pumps with motor) ግዢ ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው፡፡

12. ጽ/ቤቱ ጨረታው እንደ አስፈላጊነቱ ከእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13, የሚቀርበው ጨረታ ዶክሜንት ሎት ሁለት

13.1 ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው ፖስታ አሽጎ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም

13.2 ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው ፖስታ አሽጎ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል ፡፡

14. ፅ/ቤቱ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ ፡- ትግራይ መቐለ

መቐለ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 034 4407 335 /0921 588 220
የመቐለ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15ኛው ቀን 2019 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-16 12:00
  • Bid opening (note): በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15ኛው ቀን 2019 ዓ/ም 4፡30 ሰዓት
  • Region: Tigray
  • Publishing entity: Mekelle City Water Service Office
  • Bid bond: 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 2000 (ሁለት ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T09:05:04.000Z
← Back to all tenders