Accounting and Auditing, Accounting System Design
የጆሽዋ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/የኃ/ሥ/ማ የ2018 በጀት አመት የ(አንድ)ዓመት ኦዲት ለማስደረግ የውጭ ሂሳብ ኦዲት አድራጊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የውጭ ሂሳብ ኦዲት የጨረታ ማስታወቂያ
የጆሽዋ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/የኃ/ሥ/ማ ለ25 ዓመታት በቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በመስራት ላይ ያለ ማህበር (SACCO) ሲሆን፤
ማህበራችን የ2018 በጀት አመት የ(አንድ)ዓመት ኦዲት ለማስደረግ የውጭ ሂሳብ ኦዲት አድራጊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታማሉ ድርጅቶች በጨረታው ለመሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬት መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው፤
- በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያገኘ ብቸቦ ስተስ
- ተወዳዳሪዎች የቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር (SACO) ተመሳሳይ ዘርፍ የሂሳብ ምርመራ ልምድ እና በቂ ባለሙያ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል አዲስ ስ አበባ ዋናው ቢሮ ማግኘት ይችላሉ
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፤
- የዋጋ ማስገቢያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም ክፍት ካለው ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፤
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የሰው ሀብት እና አስተዳደር ክፍል በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ የፋይናንስ ለብቻ የቴክኒክ ለብቻ በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፤ ጨረታው ተጫራቾች ተወካዮች ባሉበት አስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 9፡00 ሰዓት ላይ መሰብሰቢያ ክፍል ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ መሙላት ይጠበቅባችኋል።
- የጨረታ አሸናፊው ጨረታውን አሸንፎ ከተዋዋለ በኋላ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይፈቀድም።
- ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አዲስ አበባ ደንበል ፊትለፊት
- በሚገኘው ዋናው ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0115582023 /0115584416 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ጆሽዋ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/የኅ/ሥ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 15:00
- Bid opening (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስረኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Joshua Savings and Loan Basic Cooperative Society Work Association
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T09:07:37.000Z