Distribution of Different products
ዳሸን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. በቀን ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል ያወጣውን ጨረታ የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜ ማራዘሙን እና የአድራሻ ለውጥ ማድረጉን ለማሳወቅ ይወዳል
Description
የጨረታ ጊዜ ማራዘሚያ እና የአድራሻ ለውጥ ማስታወቂያ
ዳሸን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. በቀን ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የዳሽን ቢራ ምርቶችን ለማከፋፈል ያወጣውን ጨረታ የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜ ማራዘሙን እና የአድራሻ ለውጥ ማድረጉን ለማሳወቅ ይወዳል።
ጨረታው የዳሸን ቢራ ምርቶችን በሚከተሉት ዋና ዋና ገበያዎች ለማከፋፈል የሚያስችሉ ብቁና ፍላጎት ያላቸው አከፋፋዮችን ለመመልመል የተዘጋጀ ነው፦ ጭሮ / አሰበተፈሪ ገበያ፣ መከንሰላም እና ደላንታ ገበያ፣ ማይጨው ገበያ፣ ቡሌ ሆራ ገበያ፣ ወረኢሉ ገበያ እና ሸዋሮቢት ገበያ.
የጨረታ ጊዜው የሚራዘመው የዳሸን ቢራ አ.ማ. ዋና መሥሪያ ቤት ወደ አዲሱ አደይ አባባ ስታዲየም አካባቢ፣ ከወርቁ ህንፃ ጀርባ መቶ ሜትረ ገባ ብሎ ወደሚገኘው አዲስ ቢሮ በመዛወር ላይ በመሆኑ እና ለሁሉም ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች በቂ ጊዜ ለመስጠት ነው።
ስለሆነም፣ የጨረታ ማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ተራዝሟል።
እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ከጳጉሜ 3 ቀን 2018 እስከ መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በዋናው የጨረታ ማስታወቂያ የተገለጹት ሌሎች የጨረታ ውሎች፣ መስፈርቶች፣ ሁኔታዎች እና መመሪያዎች በሙሉ ሳይለወጡ ይቀጥላሉ።
ስለዚህ ሁሉም ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በተጠቀሰው ጊዜ ገዝተው፣ የተሟላ የጨረታ ማቅረቢያቸውን ከመስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም. በፊት ወይም በዚያ ቀን በተወሰነው ሰዓት እንዲያቀርቡ ዳሸን ቢራ አ.ማ. ያሳስባል።
ዳሸን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ.
ለማንኛውም ጥያቄ እና ማብራሪያ [email protected] የኢሜል አድራሻን ይጠቀሙ
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/6a8c16130a538ad2ec000001
Tender details
- Deadline: 2026-09-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-16 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dashen Breweries S.C.
- Buyer TIN: 0001447387
- Published on: Reporter (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T10:24:22.000Z