Distribution of Different products

ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በወራቤ እና በቡታጅራ የኮካ -ኮላ ምርቶችን አከፋፋይ ይፈልጋል

Description

በወራቤ እና በቡታጅራ የኮካ -ኮላ ምርቶችን አከፋፋይ መሆን ለሚፈልጉ የቀረበ ጥሪ

ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ አዳማ፣ ወራቤ፣ ቡታጅራ፤ በባተ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች፤ በደሴ፤ መቀሌ፣ ሐረር፣ ድሬዳዊ እና ወላይታ የኮካ-ኮላ ምርቶችን በማከፋፈል የንግድ አጋሮቻችን መሆን የሚችሉ  አስተማማኝ እና የካፒታልም ሆነ ሙያዊ ብቃት ያላቸው የሀገር ውስጥ አከፋፋዮችን በመፈለግ ላይ ይገኛል። ይኸውም በወራቤ እና በቡታጅራ ለሚገኙ ብቁ ለሆነ አከፋፋዮችን የአጋርነት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

መሰረታዊ የተሳትፎ መስፈርቶች

ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን መሰረታዊ መስፈርቶች ማሟላት ከቻሉ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፤

  • ስራው የሚጠይቀውን የስራ ማስኬጃ ካፒታል፡ በኢትዮጵያ ብር ማቅረብ የሚችል
  • በትንሹ 350 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መጋዘን ያለው እና የመጠጥ ምርቶችን ለማከማቸት እና ለማከፋፈል ተስማሚ የሆነ ጥሩ መሰረተ ልማት ያሉት
  • በገበያ ላይ ምርቶችን በስፋት ለማሰራጨት የሚያገለግሉ እንደ የጭነት መኪና፤ ፒክአፕ እና በእጅ የሚገፉ ጋሪዎችን ማቅረብ የሚችል
  • የለስላሳ መጠጦችን እና በፍጥነት በዝቅተኛ ዋጋ ወደተጠቃሚ የሚደርሱ ምርቶችን በማሰራጨት ረገድ የተረጋገጠ ልምድ ያለው በመጨረሻም
  • የኮካ ኮላን የጥራት እና የአገልግሎት አሰጣጥ መስፈርቶችን በሚገባ አሟልቶ ከድርጅታችን ለመግዛት እና ለማከፋፈል ፈቃደኛ የሆነ እና አቅሙ ያለው

የቴክኒክ እና የፋይናንስ ብቃቶች

ፍላጎቱ ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  • የለስላሳ መጠጦችን እና በፍጥነት በዝቅተኛ ዋጋ ወደተጠቃሚ የሚደርሱ ምርቶችን በማሰራጨት ረገድ የተረጋገጠ ልምድ ያለው እና ማሳየት የሚችል
  • በገበያው ላይ የሚኖረውን ትልቅ የምርት ፍላጎት መሸፈን የሚችል የተደራጀ የሎጂስቲክስ እና መሠረተ ልማት ያለው
  • ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና በኢትዮጵያ ውስጥ መጠጦችን ለማከፋፈል የሚያስፈልጉትን ህጋዊ ቅድመ ሁኔታዎች ያሟላ እና ማቅረብ የሚችል
  • የማከፋፈያ ሥራው ከመጀመሪያው ከሚጠበቀው በላይ ቢያድግ ካለው ሀብት ወይም ከፋይናንስ ተቋማት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት አቅም ያለው

የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ ቅድመ ሁኔታዎች፡

  • የIT መሰረተ ልማት እና የኢንተርኔት ግንኙነት ያለው
  • ኮምፒውተር እና ስማርት ስልኮች
  • የኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ (ሲሲቢኤ በኢትዮጵያ) ሶፍትዌር ሲስተሞችን በተለይም ለሽያጭ ክትትል እና ኢንቬንቶሪ (ስቶክ) አስተዳደር የሚያገለግሉትን ለመጠቀም ዝግጁ የሆነ

የጨረታ ማቅረቢያ መመሪያዎች፤

ብቁ እና ፍላጎት ያላቸው የንግድ ድርጅቶች የሚከተሉትን የሚያጠቃልሉ ሙሉ ፕሮፖዛሎችን እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል።

  • ስለድርጅቱ እና ከዚህ ቀደም በዘርፉ ያለውን ልምድ በግልጽ የሚያሳይ ዝርዝር መገለጫ ፕሮፋይል/
  • ንግዱን ለመጀመር የሚያስችለውን የካፒታል መጠን እና የገንዘብ ድጋፍ እንዳለው የሚያረጋግጡ ትክክለኛ ሰነዶች ሊያቀርቡት ስለሚችሉት የመጋዘን እና የመጓጓዣ መሠረተ ልማት ዝርዝር መረጃ
  • በኢትዮጵያ ውስጥ አከፋፋይ ሆነው ለመስራት ህጋዊ ፈቃድ ማግኘትዎን የሚያረጋግጡ ትክክለኛ የንግድ ፈቃዶች እና ሌሎች ኦፊሴላዊ ሰነዶች

የፕሮፖዛል ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን፡ መስከረም 07፣ 2019 ዓ.ም

ፕሮፖዛል ማስገቢያ ኢሜይል አድራሻ፡

[email protected]

ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ (ሲሲቢኤ በኢትዮጵያ)

አድራሻ፡- ኮካ-ኮላ ማዞሪያ፣ ጅማ መውጫ መንገድ ላይ

ፖ.ሳ.ቁ 1346

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ ታማኝ እና ብቁ ከሆኑ የስራ አጋሮች ጋር ጠንካራ እና ውጤታማ አጋርነት ለመፍጠር ቁርጠኛ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ በሁሉም ስፍራዎች ተፈላጊ የሆነው የኮካ-ኮላ ምርታችን ለደንበኞቻችን እንዲሁም ተጠቃሚዎቻችን በሚፈልጉት መጠን እንዲደርስ የሚያስችል ቀልጣፋ አሰራርን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

Coca-Cola Beverages Africa


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-09-17 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Coca-Cola Beverages Africa
  • Published on: The Reporter (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T09:22:52.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders