Pumps, Motors and Compressors

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ የውሃ ፓምፕ ማድረጊያ የሶላር ሲስተም አቅርቦት፣ ማጓጓዝ፣ ተከላ፣ ሙከራ (Testing and Commissioning) እና ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጎ የማስረከብ ሥራ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ (HUNDEE) በDutch Relief Alliance (DRA) የፋይናንስ ድጋፍና ከCordaid ጋር በመተባበር በሚተገብረው Ethiopian Joint Response ( JR) ፕሮጀክት ሥር በቦረና ዞን፣ በዱብሉቅ ወረዳ፣ ቦኮሳ ቀበሌ የውሃ ፓምፕ ማድረጊያ የሶላር ሲስተም አቅርቦት፣ መጓጓዝ፣ ተከላ፣ ሙከራ (Testing and Commissioning) እና ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጎ የማስረከብ ሥራ በክፍት ጨረታ (Open National Competitive Bidding) ለማስፈጸም ስለሚፈልግ፣ በዚህ ዘርፍ ብቁና ተሞክሮ ያላቸውን ተጫራቾች ይጋብዛል።

የተጫራቾች መስፈርቶች

1. የ2026/2018 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ በዘርፉ የተመዘገበ ድርጅት መሆን አለበት።

2. ትክክለኛ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) እና አስፈላጊ በሆነ ሁኔታ የእሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።

3. ሕጋዊ የፋይናንስ ደረሰኝ (VAI Receipt) መስጠት የሚችል መሆን አለበት።

4. በጨረታ ሰነዱ የተገለጹትን ቴክኒካልና አስተዳደራዊ መስፈርቶች ማሟላት አለበት።

የጨረታ ሰነድ

  • የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከሁንዴ ዋና መሥሪያ ቤት መግዛት ይቻላል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security/Bid Bond) ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 3% በሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም Bank Guarantee ማቅረብ ያስፈልጋል።
  • የቴክኒክና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች በታሸገና በማኅተም በታተመ ኤንቨሎፕ በማስገባት መቅረብ አለባቸው::

የጨረታ ሰነድ መግዣና ማስገቢያ

የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አደባባይ አካባቢ፣ ከቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የሁንዴ ዋና መሥሪያ ቤት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።

የጨረታ ሰነዱን ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን የማስታወቂያው 7ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሲሆን፣ ጨረታው በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል።

የጨረታ መክፈቻ

ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በሁንዴ ዋና መሥሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።

የአሸናፊው ግዴታ

አሽናፊው ድርጅት የሶላር ሲስተሙን ወደ ፕሮጀክቱ ቦታ በማጓጓዝ፣ በመትከል፣ የሙከራ ሥራዎችን (Testing and Commissioning) በማከናወን እና ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጎ ለድርጅቱ ማስረከብ አለበት። የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ (Technical Specification) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ይሰጣል።

ልዩ ማሳሰቢያ
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ያለምንም ምክንያት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡ +251 91 339 9817/ 011-558-2328


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-09 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hundee-Oromo Grassroots Development Initiative
  • Buyer address: አዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አካባቢ፣ ያሬድ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ በቪላ ቨርዴ ሆቴል ገባ ብሎ
  • Bid bond: 3%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T11:38:29.000Z
← Back to all tenders