Kitchen Equipment
አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማኅበር የተለያዩ የወጥ ቤትና የገበታ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ማለትም ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እና የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ አስመጭዎች እና አከፋፋዮችን ለአንድ ዓመት ኮንትራት ውል በመያዝ አብሮ ለመሥራት ይፈልጋል
Description
ለአስመጭዎች እና ለጅምላ አከፋፋዮች የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማኅበር የተለያዩ የወጥ ቤትና የገበታ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ማለትም ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እና የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ አስመጭዎች እና አከፋፋዮችን ለአንድ ዓመት ኮንትራት ውል በመያዝ አብሮ ለመሥራት ይፈልጋል።
1. የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
2. የንግድ ምዘገባ ምስክር ወረቀት፣ የቲን (TIN) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚሳተፉበት ዘርፍ ብር 30,000 (ሠላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍም ሆነ በወጥ ቤትና የገበታ ዕቃዎች አቅርቦት ዘርፍ የሚሳተፉ ድርጅቶች ቀጥታ አስመጭ ድርጅት ወይም የጅምላ አከፋፋይ መሆናችሁን የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
5. ማንኛውም ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሕጋዊ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አጠገብ በሚገኘው ዋናው መሥሪያ ቤት 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
6. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፍት ይሆናል።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም
አድራሻ ስልክ 0966616161 ወይም 0911357043
አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-16
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-16 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Fana General Commodities and Hotels Business S.C
- Buyer address: ራስ መኰንን ድልድይ የቀድሞ ኢትሆፍ የአሁኑ አዲስ ፋና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ ሆቴሎች ንግድ አክሲዮን ማህበር፣
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T07:41:21.000Z