Accounting and Auditing, Accounting System Design
ዓባይ ጋርመንት አክሲዮን ማህበር የ2018 ዓ.ም. ሂሳብ ለማስመርመር (ኦዲት) ማስደረግ ይፈልጋል
Description
ማስታወቂያ
እንደሚታወቀው ድርጅታችን መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን የድርጅታችንን የ2018ዓ.ም ሂሳብ ለማስመርመር (ኦዲት) ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
መስፈርቶቹ
- የድርጅቱን ሂሳብ [FRS/GAAP መሰረት ኢዲት ለማድረግ የሚያስችል የሙያ ፍቃድ ያላቸው
- በሙያው ብቃትና ህጋዊነት ታውቀው በመንግስት የተመዘገቡ
- የዘመኑ ግብር ከፍለው ፈቃዳቸውን ያደሱ
- የኦዲትንግ የስራ ልምድ ያላቸው
- የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው
- የሂሳብ ምርመራው(ኦዲቱ) ጎንደር ፋብሪካ ቅጥር ግቢ መሆኑን ማወቅ አለበት።
መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋና ስራውን ሰርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ቀናት ውስጥ በዓባይ ጋርመንት ኢማ ማ/ጽ/ቤት አልማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 አዲስ አበባ 4 ኪሎ አካባቢ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00(ሶስት መቶ ብር)ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡በጨረታ መመሪያው መሰረት የቴክኒክ ማወዳደርያ ሰንድ፣የዋጋ ማወዳደርያ ሰነድ እና የጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) 10% የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በተለያዩ ፖስታዎች በመሙላት ጎንደር ፋብሪካ በሚገኘው ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ጎንደር በድርጅቱ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡-ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 0918 031 502/0927 555 333 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።
ዓባይ ጋርመንት አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-19 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Abay Garment
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T08:51:35.000Z