Tour and Travel

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለመኪና ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የመኪና ኪራይ አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ከታች በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ለመኪና ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የስራ ፍቃድ ያላችሁ እና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከታች በተገለጸው የጨረታ ቁጥር በኦንላይን አውቶሜሽን እየገባችሁ ሰነዱን ማየት እና መሙላት ትችላላችሁ።

የስራው አይነት

የስራው ቦታ

የጨረታው መለያ ቁጥር

ጨረታው የሚጀምርበት ቀን

የጨረታው የሚቆይበት ጊዜ

የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታው ማስከበሪያ መጠን በብር

የመኪና ኪራይ አገልግሎት

ሀዋሳ ሻሸመኔ አዶላ /ቦረና ዶሎኦዶ ቡሌ ሆራ ያቤሎ እና ሞያሌ

4287068

ጳጉሜን 02 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 0230 ሰዓት

15 ቀን

መስከረም 12 ቀን 2019 . ከቀኑ 1100 ሰዓት

መስከረም 13 ቀን 2019 . ከቀኑ 1100 ሰዓት

30,000.00

1. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለበት።

2. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው መሆን አለበት።

3. የቫት እና የቲን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።

4. በገቢዎች አስተዳደር ባለስልጣን በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ያለው እና ደብዳቤውን ማቅረብ አለበት።

5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  • ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የጨረታ ቁጥር በዚህ ሊንክ (www.ethiotelecom.et) በመግባት የጨረታውን ሙሉ መረጃ በማግኘት ጨረታውን እንዲሳተፉ እና በተጨማሪ በኢሜል እና ከኢትዮ ቴሌኮም ለአቅራቢነት የተሰጣችሁን የይለፍ ቃል መጠቀም እንዳለባችሁ እና ከዚህ ቀደም ያላወጣችሁ ስለሲስተሙ አጠቃቀም በስልክ ቁጥር 046 220 4632 ሀዋሳ በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 103 በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-22
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-09-23 17:00
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Ethio Telecom
  • Buyer TIN: 0036917337
  • Buyer address: addis ababa
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T09:00:26.000Z
  • Buyer website: https://www.ethiotelecom.et
← Back to all tenders