Food and Beverage
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰመራ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በዚህ በ2019 በጀት ዓመት የተማሪዎች የምግብ ፍጆታ የሚሆን የምግብ አቅርቦት እና ሌሎች አላቂ እቃዎች ግዥ በሀገር ውስጥ ገበያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰመራ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በዚህ በ2019 በጀት ዓመት የተማሪዎች የምግብ ፍጆታ የሚሆን የምግብ አቅርቦት ሎት 1 ሌሎች አላቂ አላቂ እቃዎች ግዥ ሎት 2 በሀገር ውስጥ ገበያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል።
1/ ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ ማወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡-
1.1 በርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
1.2 የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
1.3 የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነ
1.4 ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለበት
1.5 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈፀመ እና
1.6 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
2/ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው ሰነድ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሠመራ ሴቶች አዳሪ ት/ቤት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ድጋፍ የሥራ ሂደት 200.00 ብር/ሁለት መቶ ብር/ በመክፍል መውሰድ ይችላሉ።
3/ ተጫራቶች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል።
4/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲፒኦ(CPO) የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል። የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፈ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የውል ማስከበሪያው ይመለስላቸዋል።
5/ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ ትምህርት ቤቱ ኣይቀበልም።
6/ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ10ኛው የሥራ ቀን 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ 10፡30 ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሠመራ ሴቶች አዳሪ ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8/ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 09 36 73 84 89 / 09 36 43 54 91 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰመራ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-14
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ10ኛው የሥራ ቀን 10፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-14 16:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ10ኛው የሥራ ቀን 10፡30 ሰዓት
- Region: Afar
- Publishing entity: Semera Women's Boarding School
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T09:02:59.000Z