Land Lease & Real Estate

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር የበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የሚገኙ 5 ቦታዎች ጠቅላላ ስፋቱ 2500 ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

የሁለተኛ ዙር መሬት ሽያጭ የሊዝ

ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር የበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በበጤ ከተማ ውስጥ የሚገኙ 5 ቦታዎች ጠቅላላ ስፋቱ 2500 ካሬ ሜትር የሆነ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች፡-

  1. የጨረታውን ሰነድ በበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ቦታው የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታውን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 10 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 10 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
  5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ዞን በጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን 29/12/2018.ዓ.ም እስከ 08/01/2019 .ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 08/01/2019 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል።
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 11/01/2019 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከትይችላሉ።
  9. የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።
  10. በበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ለተጨማሪ መረጃ ፡ በስልክ ቁጥሮች 0942295292/092020660 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጅሌ ጥሙጋ

ወረዳ የበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-09-21 10:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳደር የበጤ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T09:13:04.000Z
← Back to all tenders