House and Building Sale
ወላይታ ልማት ማህበር ለንግድና መኖሪያ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ሶስተኛ ዙር የወጣ የቤት ሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ወላይታ ልማት ማህበር የቤት ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር ወልማ/003/2026
ወላይታ ልማት ማህበር ማህበሩን ለማጠናከር በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በወላይታ ዞን (ወላይታ ሶዶ፣ ቦዲቲ፣ አረካ፣ ጉኑኖ፣ በሌ አዋሳ፣ ዲምቱ፣ ሃላሌ፣ ጎጮ እና ቡጌ) ከተሞች የሚገኙ ለንግድና መኖሪያ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ለሁለተኛ እና ሶስተኛ ጊዜ ለጨረታ የሚወጡ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በሶስተኛ ዙር የግልጽ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. በጨረታ የሚሳተፉ ግለሰቦች ከሆኑ ህጋዊ መታወቂያ፣ድርጅቶች ከሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ህጋዊ የመታወቂያ ካርድ፣ ህጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ መሆን አለባቸው።
2. ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን ወላይታ ሶዶ ከሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል እና የወላይታ ልማት ማህበር ቤቶቹ ለጨረታ በወጡባቸዉ ከተሞችና ወረዳ አስተዳደሮች በሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10% ለቤቱ ሽያጭ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋ መሰረት በማናቸውም ንግድ ባንኮች የተመሠከረለት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሠራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር አያይዘው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በዕለቱ ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ታሽጎ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ9፡15 ሰዓት ወላይታ ሶዶ በሚገኘው የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል በይፋ ይከፈታል።
5. 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ቤት ኮድ በመምረጥ የመጫረቻ ሰነዳቸዉንና ዋጋ ማቅረቢያውን ሳይዘለል፣ ሳይታለፍ ስርዝ ድልዝ ሳይገኝበት በሙሉ አጠናቅቆ በመሙላት ኮፒና ኦርጂናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በሰም በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. የጨረታው ሂደት የሚከናወነው ተጫራቹ መግዛት ለሚፈልገው ቤት ያቀረበውን ጠቅላላ ዋጋና ሰነዶችን መሰረት በማድረግ ይሆናል።
8. አሸናፊ ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መግባት የሚኖርበት ሲሆን ይህን ካልፈጸመ ጨረታውን በፈቃዱ እንደሰረዘ ተቆጥሮ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
9. ተጫራቹ በጨረታው ማሸነፉን በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጨረታ ያሸነፈበትን ቤት ዋጋ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት ገንዘቡን በማህበሩ አካዉንት ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
10. በጨረታ ያሸነፉትን ቤቶች ውል ለማጽደቅ፣ ስም ለማዛወርና ማናቸውንም ተያያዥ ወጪዎች ገዥው ይሸፍናል።
11. ተጨራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቤቶቹ በሚገኙበት ከተማ ማህበሩ በሚያመቻቸው ሰዓት ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
12. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
13. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
14. የጨረታ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም።
15. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይፈቀድም።
16. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም
ስልክ ቁጥር 09 10 54 19 63/ 09 13 25 57 29 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ወላይታ ልማት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 15:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በዕለቱ ከሰዓት 9፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-21 15:15
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በዕለቱ ከሰዓት 9፡15 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Wolaita Development Association
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T08:54:37.000Z
- Source: 2merkato