Land Lease & Real Estate
ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ ለሁለገብ አገልግሎት /mixed use/ የሚዉል ሕንፃ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሕንፃ ግዥ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ሕብር 26-27-015
ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ ለሁለገብ አገልግሎት /mixed use/ የሚዉል ሕንፃ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ማንኛዉም ህጋዊ የሆነ የሕንፃ ባለቤት (ግለሰብ ወይም ድርጅት) ስለ ጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀዉን ሰነድ ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ ካለው ገንዘብ ቤት በመገኘት ጳጉሜን 03 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የጨረታ ሰነዶችን በመውሰድ መሙላትና የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ዘጠነኛ ፎቅ በሚገኘው ሰው ሃብትና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላል።
ጨረታው መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
ኩባንያዉ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 126 3434 የውስጥ መስመር 207/190 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-01 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hibret Insurance Company S.C.
- Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T11:11:30.000Z
- Source: 2merkato