House and Building Sale

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የድርድር ቤቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ 03/2026/27

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የንብረቱ ዓይነትና የሚሰጠው አገልግሎት

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

 

የቦታው ስፋት በካ.ሜትር

 

የካርታ ቁጥር

 

አበዳሪው ቅርንጫፍ

 

የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

ከተማ

/ከተማ

ቀበሌ/ወረዳ

1

የታሸገ ውሃ ማቀነባበሪያ እና መጋዘን

ሸገር

 

ሰበታ

 

አዋስ

 

6000

WLBEN/7679

 

ሆሳዕና

 

28,000,000.00

 

2

መኖሪያ ቤት G+4 ህንፃ

አዲስ አበባ

/ቀራኒዮ

ወረዳ 03

250

K04/1/47/338/389/3854/02

በቅሎቤት

30,000,000.00

3

መኖሪያ ቤት

ጎንደር

ሳንጃ

01

340

00 831

ጎንደር

1,400,000.00

4

መኖሪያ ቤት

አዳማ

-

01

180

736467/98

አዳማ

5,000,000.00

5

መኖሪያ ቤት B+G+4 ህንጻ

አዲስ አበባ

 

ቂርቆስ

 

ወረዳ 01

 

133.35 ካሜ x 4

114.01ካሜ × 1

000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA

ስታዲየም

 

65,000,000.00

 

6

መጋዘን

ሸገር

ገላን

ገላን ቀበሌ

6300

BMG/L/IA/2014

ወሎሰፈር

95,000,000.00

የጨረታው ደንቦች፡-

1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባንኩ ስታዲየም ቅ/ፍ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና ግሎባል ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ ላይ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ፎርም/ መውሰድ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በገንዘብ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ እስከ መስከረም 12 ቀን 2010 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን አለበት። ይህንንም በግልጽ ማሳየት ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራች ድርጅት ከሆነ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፣ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርበታል።

7 አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በ30 /ሠላሳ / ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ከባንኩ ጋር የሽያጭ ውል መግባት አለበት። ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብም ካሸነፈበት ገንዘብ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ እስከ 30ኛው ቀን ድረስ አስፈላጊውን የሽያጭ ውል የማይፈጽም ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ይሆናል።

9. በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ውሳኔ እንዳገኘ ተመላሽ ይደረጋል።

10. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል የትብብር ደብዳቤ ይጽፋል።

11. ለመንግስት ማንኛውም ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ንብረት በማስተላለፍ ሂደት የሚኖር ክፍያ እና ሌሎች ማንኛውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል።

12. ባንኩ ለአሸናፊው ተጫራች እንደሁኔታው ብድር ሊያመቻች ይችላል።

13. ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ኢማ. ዋናው መ/ቤት 7ኛ ወለል የስብሰባ አደራሽ ይከፈታል።

14. መረጃ እና የንብረቶቹን አጠቃላይ ሁኔታ ማየት የሚፈልግ ተጫራች ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አማ. ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በስልክ ቁጥር 011 558 1204 ወይም 011 531 8097 በመደወል እና ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 2፡00 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 – 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ድረስ መጎብኘት ይችላል።

15. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለጋራ ስኬታችን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-22
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-22 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Global Bank Ethiopia S.C.
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
  • Posted at: 2026-09-07T11:31:02.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders