Industrial Machinery Provision and Installation
የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የዘጠኝ አጋር ድርጅቶች ጥምረት ሀንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH)፤ ብሔራዊ የሴቶች በጎ አድራጎት ድርጅት (NYWOO}፣ የአዲስ አበባ ከተማ ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት (AACDCO)፣ ሪዲም ዘ ጄኔሬሽን (RTG)፣ ፌዝ ኢን አክሽን (FIA)፤ ዱካ የወጣቶች መር ድርጅት (DYLO)፣ አይ ኤር ፎር ዘ ኔሽን (ICN)፣ ቤተሳይዳ በጎ አድራጎት ድርጅት (BCO) እና ኢንዱራንስ የወጣቶች ማህበር (EYA) በ Windows of Hope Project 2026 ስር ለቆዳ እና የጨርቃ ጨርቅ ስፌት ማሽኖች አቅርቦት ብቁ፣ የሆኑ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፓርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከጷጉሜ 2, 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአጋር ድርጅቶቹ በሚመራው የቴሌግራም ቦት username አድራሻ ማለትም @WoH_bid_portalbot በኩል ወይም በጥምረቱ መሪ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሃንድ ኢን ሃንድ ቢሮ በአካል መጥተው የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያ በሃንድ ኢን ሃንድ ሆሊስቲክ ችልድረን ሰርቪስ (HinH) ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በታሽገ ኤንቨሎፕ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ከመስከረም4 እስከ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓም ከቀኑ 10፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ተጫራቾች በአንዱ የማሽን አይነት ወይም በሁለቱም መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ለእያንዳንዱ የማሽን አይነት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
የጨረታው ሣጥን መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማያስረከቡ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) በሙሉ ለጥምረቱ አባላት ገቢ ይሆናል።
ጨረታውን ለማያሸንፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል።
ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከሞሉ በሗላ በጥምረቱ መሪ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ህንድ ኢን ሀንድ ሆሊስቲክ ቺልድረን ሰርቪስ (HinH) ቢሮ (አድራሻ፡ ጄሞ ሚካኤል፣ ወደ አየርጤና መንገድ 500 ሜትር እንደተጓዙ በሚገኘው ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ 4ኛ ፎቅ ላይ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ገፅ 7 እን 8 ላይ በግልፅ እና በአፅንኦት በተገለጸው መሠረት ለእያንዳንዱ ጥምረት አባል ድርጅት ስም እንደየድርጅቶቹ የማሽን ፍላጎት መሰረት እና ብዛት ራሱን የቻለ በአጠቃላይ 11 የቴክኒክ እና 11 የፋይናንስ ፕሮፖዛሎችን ለየድርጅቶቹ በስማቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ በትኩረት በመረዳት ተገቢውን የመወዳደሪያ መልስ መሙላት ከተጫራቾች ይጠበቃል። በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች በትክክል አለመሙላት የመወዳደሪያ ውጤቱን ያስቀንሳል።
ጥምረቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 16:00
- Bid opening: 2026-09-25 09:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: HAND-IN-HAND HOLISTIC CHILDREN'S SERVICE
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T11:58:02.000Z
- Source: 2merkato